ኢራን ትናንት አርብ በግዛቷ ጥቃት ይፈፅም የነበረ ኤፍ 15 ተዋጊ የጦር ጀትን መትታ ጥላለች።
የመስኩ ባለሙያዎችና የአሜሪካ ባለስልጣናት ሴቱ ኤፍ 15 መሆኑን ቢያረጋግጡም ኢራን ግን የጦር ጀቱ አሜሪካ አለኝ የምትለው ኤፍ 35 ነው እያለች ነው::
የጦር ጀቱ አብራሪና መሳሪያ ተኳሽ በዣንጥላ ዘለው የወረዱ ሲሆን የአሜሪካ ልዩ ኮማንዶዎች ወደ አራን ዘልቀው አንዱን አብራሪ ወታደር ሲያድኑት፤ ሁለተኛው ግን በዚያው አካባቢ በኢራናውያን እና በአሜሪካውያን የነፍስ አድን ኮማንዶዎች እየተፈለገ ነው።
የቴሄራን መንግስት ኢራናውያን ይህንን ኣሜሪካዊ በነፍስ ይዘው ቢያመጡለት ከፍተኛ ሽልማት እስጣለሁ ከማለቱ በተጨማሪ የራሱንም አሳሽ ወታደሮች አስማርቷል።
አሜሪካ ይህንን አብራሪ ለማግኘት ሁለት ሄሊኮፕተሮች አሳማርታ ሄሊኮፕተሮቹ በኢራን ሚሊሻዎች ቀላል መሳሪያ የተመቱ ሲሆን በውስጡ የነበሩ ወታደሮች ቆስለው ነገር ግን በሰላም ከወገን ጦር መቀላቀላቸው ነው የተሰማው።
ኢራን ሌላ የመታችውና በአንድ አብራሪ የሚነዳው ኤ 10 ተንደር ቦልት የተባለው የጥቃት አውሮፕላን ተመቶ ጉዳት ቢደርስበትም አብራሪው አውሮፕላኑን ከኢራን የአየር ክልል አስወጥቶ ክዌት ሲደርስ በዥንጥላ ዘሎ ወርዷል።
የአሜሪካ መገናኛ ብዙሃን በጦር ጀቶቹ ከነበሩ ሶስት በራሪዎች ሁለቱን ማዳን ተችሏል እያሉ ነው።
<span;>አሜሪካ ስለደረሰባት ጉዳት የተጠየቁት የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ አሁን አስተያየት አልሰጥም እያሉ ነው።
#EBS
#EBSTVNEWS
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
www.ebstv.tv
