EthiopiaNews

በኢትዮጵያ ሰነደ መዋዕለ ንዋይ ገበያ በአንድ ሳምንት ብቻ ከአንድ ቢሊዮን ብር በላይ ግብይት መከናወኑ ተነግሯል፡፡

በኢትዮጵያ ሰነደ ሙዓለ ንዋይ ገበያ በአንድ ሳምንት ብቻ ከአንድ ቢሊዮን ብር በላይ ግብይት መከናወኑን የኢትዮጵያ ሰነደ መዋዕለ ንዋዮች ገበያ ገልጿል፡፡

ከዚህ ቀደም በነበረው አሰራር በአንድ አመት ውስጥ የሚከናወነው ግብይት ከ5 ቢሊዮን ብር እንደማይዘል የተናገሩት የኢትዮጵያ የሰነደ መዋለ ንዋይ ገበያ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ጥላሁን እስማኤል አሁን ላይ የባለሃብቶች ፍላጎት እየጭመረ መምጣቱን ገልጸዋል፡፡

አሁን ላይ 5 ኩባንያዎች በኢትዮጵያ የሰነድ መዋለ ንዋይ ገበያ ዋና የግብይት መድረክ ላይ መመዝገባቸውን የጠቆሙት ስራ አስፈጻሚው ለሌሎች ስድስት ኩባንያዎች ደግሞ ቅድመ ምዝገባ ፍቃድ መሰጠቱን አመልክተዋል፡፡ ሪፖርተራችን ብሩክ አስቀናው ነው የዘገበው፡፡

#EBS
#EBSTVNEWS
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
www.ebstv.tv