EthiopiaNews

የአዋሽ ባንክ ትርፍ

  • አዋሽ ባንክ ከታክስ በፊት 40 ቢሊዮን ብር ማትረፉን አስታውቋል።

ይህም ከቀደመው ዓመት ጋር ሲነፃፀር የ11 ነጥብ 8 ቢሊዮን ብር ጭማሪ ማስመዝገቡን ባንኩ ገልጿል።

የባንኩን የተጠናቀቀው በጀት ዓመት አፈፃፀም አስመልክተው መግለጫ የሰጡት የአዋሽ ባንክ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ፀሐይ ሽፈራው የባንኩ ጠቅላላ ተቀማጭ ከ467 ቢሊዮን ብር በላይ መድረሱን አመልክተዋል።

የባንኩ ጠቅላላ ሀብት 622 ቢሊዮን ብር መድረሱን የተናገሩት ዋና ሥራ አስፈፃሚው የተከፈለ ካፒታሉ ደግሞ አምና ከነበረበት 27.9 ቢሊዮን ብር የ38 በመቶ እድገት በማሳየት 38.5 ቢሊዮን ብር መድረሱና ተናግረዋል።

በሂሳብ ዓመቱ የባንኩ ጠቅላላ ገቢ 85.37 ቢሊዮን ብር የደረሠ ሲሆን የባንኩ ጠቅላላ ወጪ ወደ 44.6 ቢሊዮን ብር ደርሷል ነው የተባለው።
ከ2 በመቶ በላይ የተበላሸ የብድር መጠን በዓመቱ ያስመዘገበው ባንኩ 2.6 ቢሊዮን ዶላር በላይ የውጭ ምንዛሪ መሰብሰቡንም ጠቅሷል።

ባንኩ በቀጣይ ዓመት በጎረቤት ሀገራት ቅርጫፎችን ከፍቶ ለመሥራት ለብሔራዊ ባንክ ጥያቄ አቅርቦ ፈቃድ እስኪያገኝ እየተጠባበቀ እንደሚገኝም በዚሁ ወቅት አስታውቋል።

ዘገባው የሪፖርተራችን ብሩክ አስቀናው ነው።