EthiopiaNews

መንግሥት የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት ለማስጠበቅ ዝግጁ ነዉ – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር)

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት የሚፈታተን ነገር ከመጣ መንግሥት የሀገሪቱን ሉዓላዊነት ለማስጠበቅ ከየትኛዉም ጊዜ በላይ ዝግጁ መሆኑን ተናገሩ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከምክር ቤቱ አባላት ለተነሱ ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ በሰጡበት ወቅት የፕሪቶሪያ ስምምነት ለትግራይ ህዝብ እፎይታን መስጠቱን ጠቅሰው፤ ከጦርነቱ በፊትና በጦርነቱ ጊዜ ተቋርጠው የነበሩ አገልግሎቶች ሙሉ በሙሉ መመለሳቸውን ገልጸዋል፡፡

በትግራይ ክልል ሰላም እያወኩ ያሉ ጥቂቶች መሆናቸውን አንስተው፤ ሰላም የሚያውኩ ኃይሎች ቤተሰቦቻቸውን ከፊሎቹን በአዲስ አበባ ቀሪዎቹን ደግሞ በውጪ ሀገራት ያስቀመጡ ናቸው ብለዋል፡፡

ትግራይ መውደም ነበረባት ብለው የሚያምኑ ኃይሎች ከፕሪቶሪያ ስምምነት በኋላ ማኩረፋቸውን ገልጸው፤ በአክራሪ ኃይሎች በየቀኑ ጦርነት ሊቀሰቅሱ የሚችሉ ትንኮሳዎች እንደሚፈጸሙ ጠቁመዋል፡፡

የትግራይ ወጣቶች በጉልበት ታፍነዉ ለሱዳን ኃይሎች መሸጣቸውን ያነሱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ እነዚህ ወጣቶች ምንም ለማያውቁት ጦርነት ህይወታቸውን እያጡ ነው ብለዋል።

የትግራይ ህዝብ የችግሩ ባለቤት ሳይሆን ገፈት ቀማሽ መሆኑን አመልክተው፤ አሁን ላይ በትግራይ ውስጥ ከሚኖር የትግራይ ተወላጅ በላይ በሌሎች የኢትዮጵያ ክፍሎች ያሉ የትግራይ ወላጆች በሰላም እና በነጻነት ህይወታቸውን እየመሩ መሆኑን አመልክተዋል፡፡

#EBS
#EBSTVNEWS
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
www.ebstv.tv