የአየር መንገዱ በረራ ወደ ሞሪሺየስ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ሞሪሺየስ የሚያደርገውን በረራ ትላንትና በይፋ አስጀምሯል።
አየር መንገዱ ወደ ሞሪሺየስ በሳምንት ሶስት ጊዜ እንደሚበር በተነገረበት በዚህ መድረክ ላይ ደሴቲቱ ለኢትዮጵያ አየር መንገድ 41ኛ መዳረሻው መሆንዋ ተነግሯል::
አየር መንገዱ ከዛሬ ሐምሌ 5 ቀን ጀምሮም አገልግሎት መስጠት እንደሚጀምር የተጠቀሰ ሲሆን በረራው ደሴቲቱን ከኢትዮጵያ እና ከመላው አፍሪካ እንዲሁም ከቀሪው ዓለም ጋር ያስተሳስራል ተብሏል።
በረራው በአፍሪካ እና በተቀሪው ዓለም መካከል ያለውን የአየር ትስስር ከማጠናከር ባሻገርም ቱሪዝምን እና የንግድ ግንኙነቶችን እንደሚያሳድግም ነው አየር መንገዱ የገለጸው።
