የአዲስ አበባ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ይሄን ያሉት ትናንት የ2018 በጀት ዓመት የዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ለከተማው ምክር ቤት ባቀረቡበት ወቅት ነው።
ከንቲባ አዳነች ባለፉት 5 ዓመታት የከተማዋን የትራንስፖርት አቅርቦት ለማሳደግ 467 አውቶቡሶች ተገዝተው ወደ ሥራ መግባታቸውን ገልፀዋል፡፡
በአሁኑ ወቅት አገልግሎት የሚሰጡ የመንግሥት አውቶቡሶችን ቁጥር ከ879 ወደ 1ሺ 628 ማደጉን ከንቲባዋ ጠቁመዋል።
ከንቲባ አዳነች በ2013 ዓ.ም 2ነጥብ 9 ሚሊዮን የነበረው የቀን ተጓጓዦች ቁጥር ወደ 4 ነጥብ 19 ሚሊዮን ከፍ ማለቱን ጠቅሰው የብዙሃን ትራንስፖርት የማጓጓዝ ድርሻም ከ9 በመቶ ወደ 41 በመቶ ማደጉን ተናግረዋል። መረጃው ከከተማ አስተዳደሩ ኮሚኒኬሽን ቢሮ የተገኘ ነው።
