በኢትዮጵያ የዋጋ ግሽበት ወደ 13.4 በመቶ ማደጉን ብሔራዊ ባንክ አስታወቀ፡፡
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ ኢዮብ ተካልኝ ይሄን ያሉት የገንዘብ ፖሊሲ ኮሚቴው ያፀደቀውን ውሳኔ አስመልክቶ ዛሬ በሰጡት መግለጫ ላይ ነው።
አመታዊ የዋጋ ግሽበት በ2018 ዓ.ም ታህሳስ ወር ነጠላ አሃዝ ገብቶ እንደነበር ያስታወሱት የብሔራዊ ባንክ ገዥው በመካከለኛው ምሥራቅ ግጭት ጋር በተያያዘ የዋጋ ግሽበት በሚያዚያ ወር ወደ 11 ነጥብ 7 በመቶ እንዲሁም በግንቦት ወር ወደ 13 ነጥብ 4 በመቶ ማደጉን ገልፀዋል።
በግንቦት ወር ለተመዘገበው የዋጋ ግሽበት ጭማሪ የምግብ ነክ 15 በመቶ እና ምግብ ነክ ያልሆነ 11 በመቶ ድርሻ መያዙን የተናገሩት ገዥው በሚቀጥሉት 6 ወራት ግሽበቱ በሁለት አሃዝ እንደሚቆይና በታህሳስ 2019 ዓ.ም ቅናሽ ሊያሳይ እንደሚችልም ገልፀዋል።
