የግብርና ሚኒስቴር ይሄን ያስታወቀው የ2018 በጀት ዓመት የሆርቲካልቸር ወጪ ንግድ አፈፃፀም እና የ2019 ዕቅድ ላይ ባደረገው ውይይት ነው።
በዚህ መሰረት በ2018 በጀት ዓመት በአበባ 412፣ በአትክልት 57 እና በፍራፍሬ 21 ሚሊየን ዶላር የተገኘ ሲሆን በአጠቃላይ 490 ሚሊየን ዶላር መገኘቱ ተገልጿል፡፡
በ2019 በጀት ዓመት የአበባ፣ የአትክልት እና የፍራፍሬ ምርቶችን ወደ ውጭ በመላክ 575 ሚሊየን ዶላር ገቢ ለማግኘት መታቀዱን ሚኒስቴሩ አሳውቋል፡፡
