EthiopiaNews

የአለም የምግብ ፕሮግራም ይሄን ያስታወቀው  በገጠመው የበጀት እጥረት ሳቢያ በኢትዮጵያ ለድጋፍ ፈላጊዎች አስፈላጊውን ድጋፍ ለማቅረብ መቸገሩን አስመልክቶ ባወጣው ሪፖርቱ ላይ ነው።

በኢትዮጵያ በአየር ንብረት ለውጥና ሌሎች ችግሮች ሳቢያ ከፍተኛ የሆነ የድጋፍ ፍላጎት መኖሩን የጠቀሰው የምግብ ፕሮግራሙ ባለፈው ሰኔ ወር ለ1 ነጥብ 8 ሚሊዮን ሰዎች 10 ሺህ 7 መቶ ሜትሪክ ቶን ምግብ እና 4 ነጥብ 5 ሚሊዮን ዶላር ጥሬ የገንዘብ ድጋፍ ማድረጉን ገልጿል።