InternationalNews

በምስራቃዊ ቻይና በተሰጋው ከባድ አውሎንፋስና ዝናብ ሳቢያ ከአንድ ሚሊዮን በላይ ሰዎች አካባቢውን ለቀው እንዲወጡ ተደርጓል።

ታይፉን ዶልፊን የተሰኘው ዝናብ የቀላቀለው ከባድ ንፋስ በደቀነው አደጋም አንድ ሺህ የሚሆኑ በረራዎች እንዲሰረዙ ተደርገዋል።

ታይፉን ዶልፊን ቀድሞ ከነበረው የአደጋ አቅም ደረጃ ዝቅ የተደረገ ቢሆንም አሁንም ከፍተኛ ጐርፍና የመሬት መንሸራተት ሊያስከትል ይችላል እየተባለ ነው።

በሰዓት 150 ኪሎሜትር የሚነፍሰው ዝናብ የቀላቀለው ንፋሱ በርካታ ከተሞችን መትቶ ነው አሁን ምስራቅ ቻይና ወዳሉት ግዛቶች የደረሰው።

ቀድሞ በደረሰባቸው ከተሞች ስላስከተለው አደጋ እስካሁን የተባለ ነገር የለም።

#EBS
#EBSTVNEWS
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
www.ebstv.tv