EthiopiaNews

የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት በ5 ሚሊየን ኢትዮጵያውያን ኮደሮች ኢኒሼቲቭ ዙሪያ ያዘጋጀው የልምድ ልውውጥ መርሐ ግብር ማካሄዱን ገለጸ፡፡

መርሃ ግብሩ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ወጣቶች የ5 ሚሊየን ኢትዮጵያውያን ኮደሮች ኢኒሼቲቭን እንዲቀላቀሉና የክረምቱ ወቅት ከመጠናቀቁ በፊት የተሳታፊዎችን ቁጥር ወደ 7 ሚሊየን ለማድረስ ሀገራዊ ጥሪ ማቅረባቸው ተከትሎ የተዘጋጀ መሆኑም ተገልጿል፡፡

በልምድ ልውውጥ መርሐ ግብሩ ላይ በዚህ ክረምት የኮደሮችን ቁጥር 7 ሚሊየን ለማድረስ በጠቅላይ ሚኒስትሩ የቀረበውን ጥሪ ተግባራዊ ለማድረግ እንደሚሰራም ተነስቷል።

‎መርሐ ግብሩ በሰው ሰራሽ አስተውሎት ላይ ባተኮረ የኤግዚቢሽን ጉብኝት የተጀመረ ሲሆን፥ በተካሄደው የፓናል ውይይት ላይ በኢኒሼቲቩ ዙሪያ ልምዳቸውንና እይታቸውን ያካፈሉ አራት ባለሙያዎችም ተሳትፈዋል።

ወጣት ተሳታፊዎች የዲጂታል ክህሎትን የተመለከቱ ጥያቄዎችን ለፓናሊስቶች አቅርበው ምላሽ ያገኙበት ሲሆን አጠቃላይ መርሐ ግብሩ ግልጽ ውይይትና የልምድ ልውውጥ የተስተናገደበት መሆኑን ጽህፈት ቤቱ ገልጿል።

#EBS
#EBSTVNEWS
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
www.ebstv.tv