InternationalNews

የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ በአሜሪካ የቀረበውን ባለ15 ነጥብ የጋዛ የሰላም ሃሳብን ውድቅ አደረጉ።

ኔታንያሁ የሰላም ዕቅዱን ውድቅ ያደረጉት ሀማስ ታጣቂ ቡድን ሙሉ ለሙሉ ትጥቅ ሳይፈታ የእኛ ወታደሮች ከጋዛ አይወጡም በሚል ነው።

ፕሬዝዳንት ትራምፕ ያቋቋሙት የጋዛ የሰላም ቦርድ ከሳምንት በፊት ሀማስም ሆነ ሌሎች የፍልስጤም ቡድኖች ትጥቅ ለመፍታት ተስማምተው ነበር።

ይሁንና ሀማስ ከባድ መሣሪያዎችን የሚያስረክበው እስራኤል በቅድሚያ በጋዛ የምትፈፅመውን ወረራ ካቆመችና አካባቢውን ለቃ ከወጣች ነው ይላል።

በሌላ በኩል የጋዛ የሰላም ቦርድ ትላንት በሰጠው መግለጫ በቀጠናው ሰላም እንዲሰፍን ባለ15 ነጥቡን የሰላም ዕቅድ መተግበር ሲቻል ብቻ ነው።

የሰላም ሃሳቡን ውድቅ ያደረገችው እስራኤል ባለፈው ጥቅምት የተደረሰውን ተኩስ አቁም ችላ ብላ በጋዛ ጥቃት እየፈፀመች ነው።

#EBS
#EBSTVNEWS
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
www.ebstv.tv