EthiopiaNews

የአሜሪካ ህዋ ሳይንስ ምርምር ተቋም (ናሳ) በአዲስ አበባ ያለውን የአየር ብክለት ሁኔታ ማስጠናቱን ይፋ አደረገ።

ናሳ በድረ ገጹ እንዳለው በተለይም ጥናቱ ያተኮረው በጥቁር ካርቦን ላይ ሲሆን  ይህ አይነቱ ብክለት የሚከሰተው በእሳት ቃጠሎ፣ በቢንዚል መኪኖች እና ሌሎች ምንጮች ነው።

ከ2022 እስከ 2025 ባሉት አመታት በተደረገው ጥናት በአዲስ አበባ አማካይ የአየር ብክለት መጠን የአሜሪካ የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ካወጣው ጤናማ የአየር ሁኔታ ደረጃ በሶስት አጥፍ ተበክሎ ተገኝቷል።

በሌላ በኩል ከተማዋም ሆነች ኢትዮጵያ የአየር ብክለትን በመከላከል አበረታች እርምጃ እየወሰደች ነው ተብሏል።