አሜሪካ ለኢትዮጵያውያን ሰጥታው የነበረው ጊዜያዊ የከለላ መብት “ቲፒኤስ” መቋረጥ ተፈጻሚ እንዳይሆን በፍ/ቤት ተጥሎ የነበረው ክልከላ መነሳቱ ተነገረ።
በአሜሪካ ቦስተን የሚገኘው የፌዴራል ፍርድ ቤት የትራምፕ አስተዳደር ለኢትዮጵያውያን የተሰጠው ጊዜያዊ የከለላ መብትን ማቋረጥ እንዲችል መፍቀዱ ነው የተነገረው።
በቦስተን የአሜሪካ የፌዴራል ዳኛ ብሪያን መርፊ የትራምፕ አስተዳደር ለኢትዮጵያውያን ያቋረጠው ጊዜያዊ የከለላ መብት እንዳይፈፀም ያገደው የፍ/ቤት ትእዛዝ መነሳቱን ተናግረዋል።
የፌዴራሉ ዳኛ ብሪያን መርፊ ውሳኔን ተከትሎ የአሜሪካ የሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስቴር ጊዜያዊ ከለላቸው የተቋረጠባቸው ዜጐች ከአሜሪካ በአስቸኳይ እንዲወጡ ሲል በኤክስ ገፁ አሳስቧል።
አሜሪካ ለኢትዮጵያ ሰጥታው የነበረውን የጊዜያዊ የከለላ መብት በፈረንጆቹ 2025 ማቋረጧን ተከትሎ የትራምፕ አስተዳደር ውሳኔ ተግባራዊ እንዳይሆን በፍ/ቤት ታግዶ መቆየቱ ይታወሳል።
አሜሪካ በፈረንጆቹ 2022 በኢትዮጵያ በነበረው የፀጥታ ችግር ሳቢያ ለኢትዮጵያውያን ጊዜያዊ የከለላ መብት ሰጥታ እንደነበር እና በዚህም ከ5 ሺ በላይ ዜጐች ተጠቃሚ እንደነበሩ መረጃዎች ያሳያሉ።ዘገባው የኤቢሲ ኒውስ ነው።
#EBS
#EBSTVNEWS
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
www.ebstv.tv
