የሃገራዊ የምክክር ኮሚሽን ዓለም አቀፍ የልማት አጋሮች ልዑካን ቡድን በምክክሩ ቦታ ተገኝቶ ሂደቱን መመልከቱን አስታወቀ፡፡
ኮሚሽኑ ይሄን ያለው የምክክሩ ሂደትን በተመለከተ ባወጣው መግለጫ ነው።
በተባበሩት መንግስታት የልማት ድርጅት እና በገንዘብ ሚኒስቴር አስተባባሪነት ለኮሚሽኑ ድጋፎችን የሚያደርጉ የተለያዩ ሀገራት ወኪሎች ልዑካን ቡድን አባላት የምክክር ጉባኤውን አሁናዊ ሂደት ተዘዋውረው ተመልክተዋል ተብሏል፡፡
አባላቱ ከጉብኝታቸው ባሻገር የሀገራዊ ምክክር ጉባኤውን ዐበይት ክንውን የተመለከተ ገለፃ በኮሚሽኑ ኮሚሽነሮች እንደቀረበላቸው ተገልጿል፡፡
