EthiopiaNews

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት በ1 ሺ 501ኛው የመውሊድ በዓል ወቅት ላይ ሊከሰት የሚችለውን ከፍተኛ የኃይል ጫና ለመቀነስ የቅድመ ዝግጅት ስራዎችን ማከናወኑን አስታወቀ።

አገልግሎቱ በቅድመ መከላከል ስራው መስመር ውስጥ የገቡ ዛፎችን የማስተካል፣ ያረጁ ምሰሶዎች የመቀየርና ሸክላ ኢንሱለተሮችን ወደ ኮምፖሳይት የመቀየር ስራ መስራቱን ገልጿል።

እንዲሁም 1 ሺ 458 ትራንስፎርመሮች እንዲሁም 2 ሺህ 150 ኪሎ ሜትር የሚረዝም መካከለኛ መስመር ላይ የቅድመ ጥገና ስራ ሲከናወን ከአቅማቸው በላይ የጫኑ 46 ትራንስፎርመሮች ተለይተው እንዳይቃጠሉ ለመከላከል አቅም የማሳደግ ስራ መሰራቱም ተጠቁሟል።

በተጨማሪም 32 አጋዥ ትራንስፎርመሮች ደግሞ በአዲስ መልክ ሲተከሉ በአዲስ አበባ ከተማ ዉስጥ 7 ከመሬት ስር የተቀበሩ ኬብል ብልሽት ያለባቸው ተለይተው ጥገና ተደርጎላቸዉ ወደ አገልግሎት እንድመለሱ ተደርጓል ነው የተባለው።

ከዚህ ጎን ለጎን በበዓሉ ዋዜማና ዕለት ሃይል መቆርረጥ ሲያጋጥም በአጭር ጊዜ ዉስጥ ችግሩን ቀርፎ አገልግሎቱን ለመመለስ በሁሉም ሪጅኖች ላይ ፈጣን አገልግሎት የሚሰጥ የስታንድ ባይ ቲም መቋቋሙን የገለጸው አገልግሎቱ በበዓሉ ዕለት በተመረጡ የአገልግሎት መስጫ ማዕከሎች የካርድ መሙላት አገልግሎት እንደሚሰጥም ተገልጿል።

ሆኖም ደንበኞች ከአገልግሎት አሰጣጥ ጋር የተገናኘ ጥቆማ ወይም መረጃ ለመስጠት የደንበኛ ግንኙነት ማዕከል አጭር የስልክ ቁጥሮችና በአቅራቢያ በሚገኝ የአገልግሎት መስጫ ማዕከል ማሳወቅ እንደሚችሉ አገልግሎቱ አስታውቋል።