EthiopiaNews

የሀገር አቀፍ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት የ2018 የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ውጤት የሚታይባቸውን አድራሻዎች ይፋ አድርጓል።

አገልግሎቱ የ2018 ትምህርት ዘመን የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ ፈተና ውጤትን ተፈታኞች ከትናንት ነሐሴ 19 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ ማየት እንደሚችሉም አሳውቋል።

ተፈታኝ ተማሪዎችም ውጤታቸውን የሚከተሉትን አማራጭ ማስፈንጠሪያዎችን በመጠቀም ማየት የሚችሉ መሆኑን ነው አገልግሎቱ የገለጸው።

አያይዞም ተፈታኞች ቅሬታ ሲኖራቸው በአካል መገኘት ሳያስፈልግ https://result.eaes.et/complaint የሚለውን ማስፈንጠሪያ በመጠቀም ቅሬታቸውን ከዛሬ ነሐሴ 19 እስከ 26/2018 ዓ/ም ከቀኑ 10፡00 ሰዓት ድረስ በማቅረብ ምላሹንም በተመሳሳይ ማስፈንጠሪያ በኩል መከታተል የሚችሉ መሆኑንም አገልግሎቱ አስታውቋል።
ውጤት የሚገለጽባቸው ማስፈንጠሪያዎች፡-
በድረ ገጽ ፡ https://result.eaes.et
ቴሌግራም፡ https://result.eaes.et/telegram
አጭር የጽሑፍ መልዕክት፡ https://result.eaes.et/sms
መረጃው ከትምህርት ሚኒስቴር የተገኘ ነው።