በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ኤርቪን ማሲንጋ እና በአፍሪካ ህብረት የአሜሪካ ልዑክ ዋልተር ፓርስ የአፍሪካ ኅብረት የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ኦሊሴጎን ኦባሳንጆ ከወቅታዊ ጉዳዮች ጋር በተያያዘ በመቐለ ያደረጉት ጉብኝት አበረታች መሆኑን ገለጹ።
ኦሊሴጎን ኦባሳንጆ እንደ ልዩ መልዕክተኛነታቸው በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ እየሰሩት ያለው ስራ እጅግ በጣም ወሳኝ መሆኑን ነው ባለስልጣናቱ የጠቀሱት፡፡
የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ኦሊሴጎን ኦባሳንጆ ከመቐለ ሲመለሱ በዚሁ ጉዳይ እንደሚመክሩም ባለስልጣናቱ በመልዕክታቸው ገልጸዋል፡፡
ልዩ መልዕክተኛው ኦሊሴጎን ኦባሳንጆ መቐለ ተገኝተው በኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ከታገደው ህውሃት ሊቀመንበር ደብረጽዮን ገብረ ሚካኤል ጋር መወያየታቸው ይታወሳል። መረጃው ከአሜሪካ ኤምባሲ የተገኘ ነው።
