የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን በኢትዮጵያ ላለፋት ስድስት ወራት ታግዶ የቆየውን የሶስት ቋሚ የዜና ወኪሎቹን የዘገባ ፈቃድ ማደሱን አስታወቀ።
ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ይሄን ያስታወቀው ከሮይተርስ የሥራ ኃላፊዎች ጋር ከተወያየ በኋላ ባወጣው መግለጫ ላይ ነው፡፡
የባለሥልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ኃይማኖት ዘለቀ በውይይቱ ሚዲያው ኢትዮጵያን አስመልክቶ ባለፉት 7 ወራት ካሰራጫቸው የሚዲያ ይዘቶች መካከል የተወሰኑት የኢትዮጵያን ህጎች፣ የመገናኛ ብዙኃን አዋጅና የብሔራዊ ጥቅም የሚጻረሩ እንደነበሩ አስታውሰው ይህ መታረም እንደሚኖርበት ነው ያሳሰቡት፡፡
የሮይተርስ ሃላፊዎች በበኩላቸው አስፈላጊዉን እርማትና ማስተካከያ የዜና ተቋሙ እንደሚያደርግ መግባባት ላይ መድረሳቸውን ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ አክሎ ገልጿል።
#EBS
#EBSTVNEWS
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
www.ebstv.tv
