የኢትዮጵያ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት በ2018 በጀት ዓመት ከ3 ነጥብ 7 ሚሊዮን በላይ ሰዎች የኮሌራ ክትባት መከተባቸውን አስታወቀ።
የጤና ኢንስቲትዩቱ ይሄን ያለው በተጠናቀቀው የ2018 በጀት ዓመት የተከናወኑ ተግባራትን በገመገመበት መድረክ ላይ ነው።
ኢንስቲትዩቱ የማርበርግ ወረርሽኝ ምላሽ ወቅት ከ20 ሚሊዮን በላይ የቤት ለቤት ጉብኝት፣ የበሽታ አሰሳና የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥራዎች ባለፈው የ2018 በጀት አመት መከናወናቸውን ገልጿል።
በዚሁ በተሸኘው የ2018 በጀት ዓመት ከ4.3 ሚሊዮን በላይ ተጓዦች በበሮች ላይ የጤና ምርመራ እንዳገኙ ነው ኢንስቲትዩቱ ያስታወቀው።
ኢንስቲትዩቱ ባለፈው የበጀት ዓመት በኮሌራ፣ በወባ፣ በዴንጊ፣ በማጅራት ገትርና በሌሎች ተላላፊ በሽታዎች ላይ የተቀናጀ የምላሽ ሥራ መከናወኑን ገልጾ ከ3 ነጥብ 7 ሚሊዮን በላይ ሰዎችም የኮሌራ ክትባት እንዲያገኙ ተደርጓል ብሏል።
መረጃው ከኢትዮጵያ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የተገኘ ነው።
