የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን የአድዋ ድልድይ በደረሰበት ጉዳት ምክንያት መዘጋቱን አስታወቀ።
ባለስልጣን መ/ቤቱ ለረጅም ዓመታት አገልግሎት ሲሰጥ የቆየው የአድዋ ድልድይ በደረሰበት ጉዳት ምክንያት በተጠቃሚዎች ላይ አደጋ እንዳያስከትል መዘጋቱን ገልጿል።
በመሆኑም ከሴቶች አደባባይ ወደ ባልድራስ ትራፊክ መብራት የሚወስደው መንገድ ከዛሬ ነሐሴ 25 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ በሁለቱም አቅጣጫ ሙሉ በሙሉ ለትራፊክ እንቅስቃሴ ዝግ ተደርጓል ተብሏል፡፡
ባለስልጣን መ/ቤቱ አሽከርካሪዎች አማራጭ መንገዶችን እንዲጠቀሙ ባለሥልጣን አሳስቧል፡፡
መረጃው ከአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን የተገኘ ነው።
