EthiopiaNews

የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ከ2013 እስከ 2017 ዓ.ም ብቻ ከ53 ቢሊዮን ብር በላይ የሚገመት የወጪና ገቢ ኮንትሮባንድ ዕቃዎችን መያዝ መቻሉን አስታወቀ።

ፌዴራል ፖሊስ ይሄን ያለው በኢትዮጵያ ብሎም በአፍሪካ ሞዴል የሕግ አስከባሪ ተቋም መሆን የሚያስችለውን ሪፎርም እያካሄደ እንደሚገኝ ባመለከተበት መግለጫው ላይ ነው።

ሕገ-ወጥ የገንዘብ ዝውውርን በመከላከል፣ የኑሮ ውድነትን ለማባባስ የሚሞክሩ አላስፈላጊ ንብረት አከማቾችን በቁጥጥር ሥር በማዋል እና ወጣቶችን ከሕገ-ወጥ የሰዎች ዝውውር በመታደግ ለሀገር ኢኮኖሚ መረጋጋት እና ለዜጎች ደህንነት ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያበረከተ መሆኑንም ነው የገለጸው፡፡