EthiopiaNews

የትምህርት ሚኒስቴር የፌዴራል ልዩ አዳሪ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የተማሪዎች የፈተና ጊዜ በአንድ ቀን ማራዘሙን አስታወቀ።

ሚኒስቴሩ ይሄን ያለው በፌዴራል ልዩ አዳሪ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ለመማር ተመዝግበው ፈተና በመጠባበቅ ላይ ላሉ ተማሪዎች ባወጣው መግለጫ ነው።

ሚኒስቴሩ አንዳንድ ተማሪዎች የመፈተኛ ቦታቸውን ባለማወቃቸው ምክኒያት ቀድሞው የወጣውን የፈተና መርሃ ግብር በአንድ ቀን ማራዘሙን ገልጿል።

ሚኒስቴሩ ስለሆነም ነሐሴ 28/2018 ዓ.ም የሙከራ ፈተና እና ነሐሴ 29/2018 ዓ.ም ዋናው ፈተና እንደሚሰጥ አስታውቋል።

ሚኒስቴሩ በመሆኑም ተፈታኝ ተማሪዎች በአዲሱ መርሃ ግብር መሰረት ከጠዋቱ 2:30   በተመደቡባቸው ጣቢያዎች ራሳቸውን የሚገልጽ መታወቂያ በመያዝ እንዲፈተኑ አሳስቧል።

👉መረጃው ከትምህርት ሚኒስቴር የተገኘ ነው።