EthiopiaNews

በግብርና ምርት ወጪ ንግድ ዘርፍ ከ4 ነጥብ 5 ቢሊዮን ዶላር በላይ የውጭ ምንዛሬ ማግኘት መቻሉን የግብርና ሚኒስቴር ገለጸ፡፡

ይህ የተገለጸው የግብርና ዘርፍ የ2018 ዓ.ም የስራ አፈጻጸምና የ2019 በጀት ዓመት ዕቅድ ላይ ውይይት በተደረገበት ወቅት ሲሆን በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ከ33 ነጥብ 5 ሚሊዮን ሄክታር በላይ መሬት በተለያዩ ሰብሎች በማልማት ከ1 ነጥብ 85 ቢሊዮን ኩንታል በላይ ምርት መሰብሰብ ተችሏል ተብሏል።

ከዚህ ጎን ለጎን ከ20 ሚሊዮን ኩንታል በላይ የአፈር ማዳበሪያ በማቅረብና በማሰራጨት አርሶ አደሮቻችን የተሟላ የግብርና ግብዓት ተጠቃሚ እንዲሆኑ ተደርጓል ነው የተባለው።