ኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት የምትጠቀመውን የኢኮኖሚ ትንበያ ሞዴል ልትቀይር መሆኑን የአለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት ገለጸ።
ተቋሙ ይሄን ያለው ኢትዮጵያ እየተጠቀመች ያለው የኢኮኖሚ ትንበያ ሞዴል ለመቀየር ቴክኒካዊ ድጋፍ እያደረገ መሆኑን አስመልክቶ ባወጣው ሪፖርቱ ላይ ነው።
ከወራት በኃላ ኢትዮጵያ ነባራዊ የኢኮኖሚ ትንበያ ሥርዓትን ልትተገብር መሆኑን የጠቀሰው ሪፖርቱ ይህ ሞዴል ሀገሪቱ ስትጠቀምበት የነበረውን በሂሳብ መዛግብት አያያዝ ላይ ብቻ ከተደገፈ የኢኮኖሚ ትንበያ ሥርዓት ወደ ተለዋዋጭና በንድፈ-ሐሳብ ላይ ወደተመሰረተ የትንበያ ሞዴል እንድትሸጋገር ይረዳታል ነው ያለው።
