EthiopiaNews

የዓለም አቀፉ የፋይናንስ ኮርፖሬሽን በኢትዮጵያ የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ እንዲቀጥል የገንዘብ ሚኒስትሩ አህመድ ሽዴ ጠይቀዋል፡፡

ሚኒስትሩ ይህንን ጥያቄ ያቀረቡት ከዓለም አቀፉ የፋይናንስ ኮርፖሬሽን ማኔጂንግ ዳይሬክተር ማክታር ዲዮፕ ጋር በኢትዮጵያ ያለውን የግል ኢንቨስትመንት ለማሳደግ እና ትብብርን ለማጠናከር በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ በተወያዩበት ወቅት ነው።

በውይይቱ ወቅት ሚኒስትሩ የኢትዮጵያ መንግሥት እየተገበረ ያለው የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ለኢንቨስትመንት ምህዳሩ ማደግ አስተዋጽኦ እያደረገ መሆኑንም ገልጸዋል፡፡

ዓለም አቀፉ የፋይናንስ ኮርፖሬሽን በኢትዮጵያ በግብርና፣ በማኑፋክቸሪንግ፣ በፋይናንስ አገልግሎት፣ በጤና፣ በቱሪዝምና በቴሌኮሙኒኬሽን ዘርፎች የ500 ሚሊዮን ዶላር የኢንቨስትመንት እንቅስቃሴ እንዳለውም ተገልጿል፡፡