የፍትህ ሚኒስቴር በክልሎች በየመኖሪያ ቤት ኪራይ፤ የውል ማረጋገጥና ምዝገባ ሥራ ተሟላ ሁኔታ አለማከናወኑን ገለፀ፡፡
ሚኒስቴሩ ከመኖሪያ ቤት ኪራይ ቁጥጥር እና አስተዳደር አዋጅ አፈጻጸም ጋር በተያያዘ ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት ባካሄደበት ወቅት፤ በክልልሎች የኪራይ ዋጋ ጭማሪ አሰራር ሥርዓት አለመዘርጋቱ እና ተከታታይ ድጋፍና ክትትል አለማድረጉን ነው የገለፀው፡፡
እንዲሁም በክልሎች የተሟላ አደረጃጀት እና በቂ የሰው ኃይል አለማኖር፣ የተቆጣጣሪ አካላት ግንዛቤና ቁጥጥር አነስተኛ መሆን፣ እንዲሁም በተወሰኑ ክልሎች አቤቱታ ሰሚ ኮሚቴዎች አለመቋቋሙም ተነግሯል፡፡
ሚኒስቴሩ በአጠቃላይ አዋጁን የጣሱ አካላት ላይ ጥቆማዎችን በመቀበል የቅጣት ውሳኔ የማስተላለፍና የማስፈጸም ሥራ መሠራቱ እንደ መልካም ጅምር የሚነሳ መሆኑን በመግለፅ በክትትሉ የታዩትን ክፍተቶች ለማረም የሚረዱ ምክረ-ሀሳቦችን ተግባራዊ ማድረግ ይገባል ብሏል፡፡
