ብሔራዊ ባንክ ትናንት ጳጉሜ 4 2018 አ.ም ባካሄደው የውጭ ምንዛሬ ጨረታ አንዱን ዶላር በ160 ብር ከ53 ሳንቲም መሸጡን አስታወቀ።
ባንኩ ትናንት ባደረገው የውጭ ምንዛሬ ጨረታ 20 ባንኮች መሳተፋቸው እና በጨረታው የተሳተፉት 20ዎቹም ባንኮች አሸናፊ መሆናቸውን ገልጿል።
ብሔራዊ ባንክ ከዚህ ቀደም ካካሄደው የውጭ ምንዛሬ አንጻር የአንዱ ዶላር ዋጋ ላይ የዐ ነጥብ 33 ሳንቲም ጭማሪ አለው፡፡
ባንኩ ካወጣው የ125 ሚሊየን ዶላር የውጭ ምንዛሬ ጨረታ ውስጥ 5 ሚሊየን ዶላሩን ሳይሸጥ ቀርቷል።
ባንኩ በቀጣይ የሚያደርገውን የውጭ ምንዛሬ ጨረታ ከዚህ ቀደም ባወጣው መርሃ ግብር መሰረት አሳውቃለሁ ብሏል።
ብሔራዊ ባንክ ከ15 ቀናት በፊት ባደረገው የውጭ ምንዛሬ ጨረታ አንዱን ዶላር 160 ብር ከ20 ሳንቲም መሸጡ ይታወሳል።መረጃው ከብሔራዊ ባንክ የተገኘ ነው።
