የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በመጪዎቹ 3 ወራት 840 ሚሊዮን ዶላር የውጭ ምንዛሪ ጨረታ ለባንኮች እንደሚያቀርብ አስታወቀ፡፡
ባንኩ ዛሬ ባወጣው መግለጫ በየ ሁለት ሳምንቱ የሚካሄዱ 6 የጨረታ መርሃ ግብሮች እንደሚኖሩ ይፋ ያደረገ ሲሆን በእያንዳንዱ መርሃ ግብር ወቅት 140 ሚሊዮን ዶላር ለጨረታ እንደሚቀርብም ገልጿል፡፡
ባንኩ በመጪው ማክሰኞ 140 ሚሊዮን ዶላር የውጭ ምንዛሪ ለባንኮች እንደሚያቀርብም ጠቅሷል፡፡
ብሄራዊ ባንኩ ባለፉት ሶስት ወራት 1 ቢሊዮን ዶላር ገደማ የውጭ ምንዛሪ ለባንኮች ማቅረቡም የሚታወስ ነው፡፡
