የእስራኤል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ሳር ከኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቲዮስ ጋር ኢትዮጵያ ውስጥ ስላለው ወቅታዊ ሁኔታ በስልክ መወያየታቸው ተገለጸ፡፡
በውይይታቸውም ስለ ኢትዮጵያ አንድነትና መረጋጋት አስፈላጊነት እንዲሁም በአፍሪካ ቀንድ ሰላምና መረጋጋትን አስመልክቶና ስላለን የጋራ ጥቅም ጭምር መነጋገራቸውም ተጠቅሷል፡፡
እስራኤል ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን የረጅም ጊዜ ጥብቅ ወዳጅነት እጅግ ከፍ አድርጋ የምትመለከት መሆኑን የገለጹት የእስራኤል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ሳር ሀገራቸው ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን ግንኙነት ይበልጥ ለማጠናከርም በትብብር ትሰራለች ብለዋል።
