EthiopiaNews

ሁሉም ሚኒስትሮችና ሚኒስትር ዲኤታዎች ለአንድ አመት ያክል ከፍተኛ ሚስጥራዊ ክትትል ሲደረግባቸው እንደነበር ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ገልጸዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ በዛሬው እለት ሹመታቸው የፀደቀላቸውን የሚኒስትሮች መመዘኛ አስመልክቶ ለምክር ቤት አባላት ባደረጉት ንግግር ሁሉም ሚኒስትሮችና ሚኒስትር ዲኤታዎች ቢያንስ ላለፉት አንድ አመታት ከፍተኛ ሚስጥራዊ ክትትል ሲደረግባቸው እንደነበር አስታውቀዋል።

ሚኒስትሮች በሌብነት የተሳተፉ እንዳይሆኑ ከፍተኛ ጥንቃቄ መደረጉን ያነሱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሲደረግባቸው የቆየው ክትትልም በሀገር ውስጥና በውጪ ያላቸውን እንቅስቃሴ ያጠቃለለ ሲሆን ቤተሰቦቻቸውን ጨምሮ ከሚያገኙቸው ሀብታሞች ጋር በሙሉ የመረጃ ክትትል ይደረግ ነበር ብለዋል፡፡

በዚህም መሰረት በልዩ ትኩረት ግምገማዎች መደረጉን ገልፀው ሹም ሽር የተካሄደው ያለምክንያት  እንዳልሆነም  ጠቅሰዋል፡፡

ነገርግን አንድ ሚኒስትር ራሱ ሌባ ላይሆን ይችላል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ በከባቢው ያለውን ሌብነት የመቆጣጠርና ጥቆማ ሲሰጠው እንደ ግብዓት ወስዶ የመፈተሽ አንዱ ለተሿሚዎች መመዘኛ እንደነበር አንስተዋል።