በስለት መወጋትና የመረጃ መረብ ማስፈራሪያ የበረከተባት ፖላንድ 24 ሺህ ተጨማሪ የፖሊስ ኃይል አሰማራች።
መንግስት ከዚህ ውሳኔ የደረሰው በአራት ቀናት ውስጥ ሦስት ሰዎች በስለት ተወግተው ከሞቱና ከ12 በላይ ሌሎች ሰዎች በተለያየ ደረጃ ከቆሰሉ በኋላ ነው።
ከዚህ በተጨማሪ በመረጃ መረብ ላይ ተጨማሪ በስለት የመወጋት ማስፈራሪያዎች በመበራከታቸው ፖላንዳዊያን ስጋት ውስጥ መግባታቸው ነው የተገለፀው።
በዚህ ስጋት ምክንያት አንዳንድ ትምህርት ቤቶች ሲዘጉ ወላጆችም ሕፃናቱን በቤት ማስቀረት መርጠዋል።
ፖሊስ ወንጀሉን ለመከላከል እስካሁን 80 ሺህ የትምህርት ተቋማትን መፈተሹንና 135 ሰዎችን ማሰሩን ገልጿል።
