ትምህርት ሚኒስቴር በፌዴራል ልዩ አዳሪ 2ኛ ደረጃ ት/ቤቶች ለተመዘገቡ ተማሪዎች የመግቢያ ፈተና የሚሰጥበትን ቀን ይፋ አደረገ።
ሚኒስቴሩ ይሄን ያለው ዛሬ ባወጣው መግለጫ ነው።
በፌዴራል ልዩ አዳሪ 2ኛ ደረጃ ት/ቤቶች ለተመዘገቡ ተማሪዎች የመግቢያ ፈተና የሚሰጠው ጥቅምት 7 ቀን 2019 ዓ.ም መሆኑን ሚኒስቴሩ ገልጿል።
ሚኒስቴሩ ፈተናው የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና በኦንላይን በተሰጠባቸው የፈተና ማዕከላት እንደሚሰጥ ገልጿል።
ተማሪዎች ፈተናውን አልፈው በሚመደቡባቸው ትምህርት ቤቶች ለመማር ፈቃደኛ መሆን እንደሚጠበቅባቸው ተገልጿል።
