ዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት አይ.ኤም.ኤፍ ለኢትዮጵያ ሁሉን አቀፍ የኢኮኖሚ ሽግግርና እድገት የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታወቀ።
በታይላንድ ባንኮክ እየተካሄደ በሚገኘው የአይ.ኤም.ኤፍ እና ዓለም ባንክ ዓመታዊ ስብሰባ ላይ እየተሳተፈ የሚገኘውን የኢትዮጵያ ልዑካን ቡድን የሚመሩት የብሔራዊ ባንክ ገዥ ኢዮብ ተካልኝ ከዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት ምክትል ማኔጂንግ ዳይሬክተር ናይጀል ክላርክ ጋር ተወያይተዋል።
በዚሁ ጊዜም ኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ሪፎርም አጀንዳን ለማስቀጠል ያላት ቁርጠኝነት ያደነቁት ናይጀል ክላርክ አይ.ኤም.ኤፍ ከኢትዮጵያ ጋር ያለውን አጋርነት ይበልጥ ለማጠናከርና ለሀገሪቱ ሁሉን አቀፍ የኢኮኖሚ ሽግግርና እድገት የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል፡፡
