EthiopiaNews

የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት የመስከረም ወር 2019 አ.ም የዋጋ ግሽበት 14.9 በመቶ ሆኖ መመዝገቡን አስታወቀ።

አገልግሎቱ ይሄን ያለው ዛሬ ባወጣው መግለጫ ነው።

በመስከረም ወር 2019 አ.ም የተመዘገበው የዋጋ ንረት ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወር ከተመዘገበው የ13 ነጥብ 2 በመቶ ጋር ሲነጻፀር ጭማሪ ማሳየቱን ነው አገልግሎቱ የገለፀው፡፡

የምግብ እና አልኮል ያልሆኑ መጠጦች ዋጋ 14. 8 በመቶ ፣ስጋ በ22 በመቶ ፣ አትክልት በ11.4 በመቶ ፣ እንቁላል 17.7 በመቶ ፣ ፍራፍሬ 18 .5 በመቶ ፣ ዘይት እና ቅቤ 18 .2 በመቶ እና የምግብ ምርቶች 19.1 በመጨመራቸው የተመዘገበ ጭማሪ መሆኑን የአገልግሎቱ መረጃ ያመለክታል።

ምግብ ነክ ያልሆነ የዋጋ ግሽበት 15 ነጥብ 1 በመቶ የደረሰ ሲሆን ትራንስፖርት 16 በመቶ ፣ ምግብ ቤቶች እና ሆቴሎች 15. 3 በመቶ ፣ኮሙዩኒኬሽን 9.6 ትምህርት 17.8 በመቶ ፣ ጤና 10.9 በመቶ እንዲሁም ሌሎች እቃዎች እና አገልግሎቶች 17.6 በመቶ ጨምሯል ተብሏል።

ባለፈው የ2018 አ.ም ነሐሴ ወር አጠቃላይ የዋጋ ንረት 15 ነጥብ 1 ሆኖ መመዝገቡ ይታወሳል።