EthiopiaNews

የመንግስታቱ ድርጅት የህፃናት መርጃ ( ዩኒሴፍ) ልዩ ልዩ የሰብአዊ ድጋፍ የጫኑ መኪኖች መቐለ መግባታቸውን አስታወቀ።

ዩኒሴፍ ይሄን ያለው በኤክስ የትስስር ገፁ ባጋራው የቪዲዮ መልዕክት ነው።

መቐለ የገቡት መኪኖች አስፈላጊ መድሃኒቶች ፣ የእናቶች እና የህፃናት የጤና መጠበቂያዎች ፣አልሚ ምግቦች እና የትምህርት ቁሳቁሶች የጫኑ ናቸው ተብሏል።

የሰብአዊ ድጋፉ በግጭቱ ለተጎዱ ቤተሰቦች የሚውል ነው ተብሏል።