EthiopiaNews

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የፓን አፍሪካ የክፍያ ሥርዓት መቀላቀሉ ተነገረ።

የፓን አፍሪካ የክፍያ ሥርዓት (ፒኤፒ ኤስ ኤስ ) አባል አገራት በራሳቸው መገበያያ ገንዘብ አማካኝነት በቀጥታ የተለያዩ ግብይቶችን እንዲፈጽሙ የሚያስችልና የድንበር ተሻጋሪ የክፍያ ወጪዎችን በመቀነስ ንግድን ለማቀላጠፍ የሚያስችል ሥርዓት ነው።

የብሔራዊ ባንክ ገዥ ኢዮብ ተካልኝ (ዶ/ር) ኢትዮጵያ የፓን አፍሪካ የክፍያ ሥርዓት አባል መሆኗ የሃገሪቱ የፋይናንስ ስርአት ለማዘመን የሚደረገውን ጥረት የሚያሳይ እና ከሌሎች የአፍሪካ ሀገራት ጋር ያለው የኢኮኖሚ ትስስር እንዲጠናከር የሚረዳ ነው ብለዋል።

በፈረንጆቹ 2022 የተመሰረተው የፓን አፍሪካ የክፍያ ሥርዓት ኬንያን ጨምሮ 15 አገራት በአባልነት ያቀፈ ነው።

በዚሁ የፓን አፍሪካ የክፍያ ሥርዓት ከ150 በላይ ባንኮች እንዳሉበት የሮይተርስ ዘገባ ያሳያል።