የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የ2019 ዓ.ም የሐጅ ጉዞ ምዝገባ የፊታችን ሐሙስ ጥቅምት 12 ቀን 2019 እንደሚጀምር አስታወቀ።
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የ2019 ዓ.ም የሐጅ ጉዞ ምዝገባ አስመልክቶ በዛሬው እለት መግለጫ ሰጥቷል።
የምዝገባ ሂደቱ ቴክኖሎጂን በሚጠቀሙ በ33 የሐጅ ምዝገባ ማዕከላት በኩል እስከ ጥር 10 ቀን 2019 ዓ.ም ድረስ እንደሚቆይ ተገልጿል።
ጠቅላይ ምክር ቤቱ የዘንድሮው የሃጅ መስተንግዶ የጉዞ ዋጋ 827 ሺህ ብር እንዲሆን መወሰኑን ገልጿል።
