EthiopiaNews

የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የኢትዮጵያ ስራ ገበያ መረጃ ፕሮጀክት ጽ/ቤት ሥራ አስኪያጅ፣ የሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ኃላፊዎች፣ ሠራተኞች እና የተለያዩ ግለሰቦች ላይ የከባድ ሙስና እና በወንጀል የተገኘ ገንዘብን ሕጋዊ አስመስሎ በማቅረብ ወንጀል ክስ ተከሰሱ።

ሥራ አስኪያጅ የነበረው ብርሀኑ አለቃ አስገዶም የተሰጠውን ሥልጣን ያለአግባብ በመገልገል ከአንድ ቢሊየን አንድ መቶ ሰላሳ አራት ሚሊየን ብር በላይ ተገቢ ያልሆነ ጥቅም ያገኘ በመሆኑ እና በተደራራቢ ከባድ የሙስና ወንጀል ክስ ቀርቦበታል ተብሏል።

በተመሳሳይም የተቋሙ ሠራተኞች፣ የሠራተኛና አሠሪ አገናኝ ኤጀንሲ ባለቤቶች እና ሌሎች ግለሰቦች ጨምሮ 13 ሰዎች ላይ 16 ክሶች እንደቀረቡባቸው ፍትህ ሚኒስቴር ገልጿል፡፡

የቀረበውን ክስ ለመስማት የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 5ኛ ወንጀል ችሎት ለጥቅምት 11 ቀን 2018 ዓ.ም ቀጠሮ መስጠቱንም ሚኒስቴሩ ጠቅሷል፡፡