EthiopiaNews

የህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አህመድ ሽዴ በሀገራዊ ምክክር ጉባኤ የቀረቡ ምክረ ሃሳቦች ተፈጻሚ እንዲሆኑ በትኩረት እንደሚሰራ ተናገሩ።

አፈጉባዔው ይሄን ያሉት የህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት ለኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ኮሚሽነሮች ባዘጋጀው የእውቅና እና ምስጋና መርሃ ግብር ላይ ነው።

አፈ ጉባኤው በኢትዮጵያ ለዘመናት ሲንከባለሉ የመጡ ችግሮችን በምክክርና በመግባባት እንደሚፈቱ ያሳየ ትልቅ ውጤት የተገኘበት መሆኑንም ጠቅሰዋል።

አራት ሺህ ኢትዮጵያዊያን መክረው ለሀገር ግንባታ መሰረት አኑረዋል ያሉት አፈ ጉባኤው፤ ለሰለጠነ የፖለቲካ ሥርዓት ግንባታ አወንታዊ አስተዋጽኦ እንደሚያበረክት አብራርተዋል።

የኮሚሽኑ አባላት በሥራቸው ላሳዩት የላቀ የሙያ ሥነ-ምግባር፣ የሀገር ፍቅር እና የሕዝብ አገልጋይነት ስሜት ምስጋና አቅርበዋል።

በቀጣይም በምክክሩ የቀረቡ ምክረ ሃሳቦች ተግባራዊ እንዲሆኑ እንዲሁም ወደ ህግ የሚቀየሩ ጉዳዮችም ተቀይረው ስራ ላይ እንዲውሉ ምክር ቤቱ አበክሮ እንደሚሰራም አረጋግጠዋል።