ኒጀር ከምስራቃዊ ሊቢያ መሪዎች ጋር ወታደራዊ የትብብር ስምምነት ተፈራረመች፡፡
ኒጀር ከምሥራቅ ሊቢያው ወታደራዊ አዛዥ ጄኔራል ካሊፋ ሀፍታር ጋር ወታደራዊና የሁለትዮሽ ግንኙነታቸውን ለማጠናከር የሚያስችል ስምምነት ተፈራርማለች፡፡
በጠቅላይ ሚኒስትር አሊ ማሃማን ላሚን ዘይን የተመራው የኒጀር ከፍተኛ የፖለቲካ እና ወታደራዊ ልዑክ፣ የሀፍታር አስተዳደር ማዕከል ወደ ሆነችው ቤንጋዚ በማቅናት በተለያዩ ዘርፎች ላይ አብሮ ለመሥራት ተስማምቷል፡፡
ኒጀር ከሊቢያ ጋር ከ340 ኪሎሜትር በላይ የጋራ ወሰን አላት፡፡
ምንም እንኳ ሊቢያ እ.ኤ.አ ከ 2014 ጀምሮ በተባበሩት መንግስታት እውቅና የተሰጠው በጠቅላይ ሚኒስትር አብዱልሃሚድ ድቤባ በሚመራው የትሪፖሊ መንግስት እና በምስራቅ የአገሪቱ ክፍል በሚገኘው ተፎካካሪ አስተዳደር መካከል የተከፋፈለች ቢሆንም የኒጀር ጉብኝት ከቤንጋዚ ጋር መቃረብ መጀመራቸውን ያሳያል ተብሏል፡፡
እ.ኤ.አ በ2011 ከሙሃመድ ጋዳፊ መውደቅ በኋላ በምሥራቅ እና ምዕራብ ተከፍላ የምትገኘውን ሊቢያን ለማዋሃድ በቱርክ አዘጋጅነት አዳዲስ የሰላም ውይይቶች ሊኖሩ እንደሚችሉ ተጠቁሟል።
