EthiopiaNews

2ተኛው የአፍሪካ ፖለቲካ ፓርቲዎች ጉባኤ በአዲስ አበባ መካሄድ ጀምሯል።

አህጉራዊ አጀንዳዎችን በታላቅ ድምቀት የሚመራው ሁለተኛው የአፍሪካ ፖለቲካ ፓርቲዎች ጉባኤ ለእድገት ማስተዳደር የፖለቲካ ፓርቲዎች እንደ ኢኮኖሚያዊ መፃኢ እድል ነዳፊዎች በሚል መሪ ቃል ነው የሚካሄደው።

በሚካሄደው በዚህ ጉባኤ ላይ ከተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት የተውጣጡ የፖለቲካ ፓርቲ መሪዎች፣ የሀገር መሪዎች፣ ፖሊሲ አውጪዎች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በአዲስ አበባ ተገኝተዋል።

በጉባኤው ላይ የፖለቲካ ፓርቲዎች ከተለመደው የሥልጣን ሽሚያ ወጥተው፣ የሀገር በቀል ኢኮኖሚ፣ የግብርና፣ የኢንዱስትሪ እና የዲጂታል ልማት መሪዎች በመሆን አህጉራዊ ትራንስፎርሜሽኑን ማፋጠን የሚችሉበት አዲስ ፍሬሚንግ እና የፖሊሲ አቅጣጫ ይመከራል ነው የተባለው።

ጉባኤው ዛሬ በሚካሄዱ ቅድመ ጉባኤ መርሐ ግብሮች ይጀምራል የተባለ ሲሆን በዚህም የአፍሪካ የሴቶች አመራር ጉባኤና የአፍሪካ ወጣቶችና ፖለቲካ ፎረሞች መካሄድ ጀምሯል።

እነዚህ መድረኮች ሴቶችና ወጣቶች በፖለቲካ ተሳትፎ፣ በአመራርና በአፍሪካ የልማት አጀንዳ ላይ ሐሳብ እንዲለዋወጡ ዕድል የሚፈጥር መሆኑ ተመላክቷል።