EthiopiaNews

ዲፕሎማቶችና የዓለም አቀፍ ተቋማት ተወካዮች በትግራይ ክልል የቀድሞ ታጣቂዎች የተሀድሶ ማዕከል ምልከታ ማድረጋቸው ተገልጿል።

የተባበሩት መንግሥታት ተወካዮችና በኢትዮጵያ የተለያዩ ሀገራት አምባሳደሮች በትግራይ ክልል የሚገኘውን የቀድሞ ታጣቂዎች ተሀድሶና መልሶ ማቋቋም ስልጠና ማዕከል የጎበኙ ሲሆን በአሁኑ ወቅት 5 ሺህ 500 የቀድሞ ታጣቂዎች በማዕከላቱ የተሀድሶ ስልጠና እየወሰዱ ይገኛሉ ተብሏል።

በክልሉ ቀደም ሲል የተሀድሶና መልሶ ማቋቋም ስልጠና ሲሰጥበት የቆየው የመቀሌ ማዕከል የቀድሞ ታጣቂዎችን ተቀብሎ እያስተናገደ እንደሚገኝ ተገልጿል።

የተሀድሶ ስልጠናው የቀድሞ ታጣቂዎችን ወደ ማህበረሰቡ በማቀላቀል፣ መደበኛ ህይወታቸውን እንዲመሩ ከማስቻሉ ባሻገር ለዘላቂ ሀገራዊ ሰላም ግንባታ አዎንታዊ አስተዋፅኦ እያደረገ መሆኑ ተመልክቷል።

በጉብኝቱ የብሔራዊ ተሀድሶ ኮሚሽን ኮሚሽነር ተመስገን ጥላሁንን ጨምሮ የኮሚሽኑ አመራሮች ተገኝተዋል።