EthiopiaNews

ኢትዮጵያ እና ቻይና ለኢትዮ-ጅቡቲ ባቡር መስመር ተጨማሪ ሥራዎች የሚውል የ15 ሚሊየን ዶላር የድጋፍ ስምምነት መፈራረማቸውን የገንዘብ ሚኒስቴር አስታወቀ።

ሚኒስቴሩ ይሄን ያለው ባወጣው መግለጫ ነው።

በስምምነቱ መሠረት የባቡር መስመሩን ዘላቂነት፣ አስተማማኝነትና የሥራ ቅልጥፍና ለማሳደግ የሚውል የ15 ሚሊየን ዶላር ድጋፍ ይደረጋል፡፡

ስምምነቱን የገንዘብ ሚኒስትር ዴኤታ ትዕግስት ፍስሃ እና በኢትዮጵያ የቻይና ኤምባሲ ከፍተኛ ዲፕሎማት ሊዩ ዚያኦጓንግ ፈርመውታል።

የገንዘብ ድጋፉ የኤሌክትሪክ ባቡሮችን ሙሉ በሙሉ ወደ ሥራ ለማስገባት የሚያስችሉ አስፈላጊ መለዋወጫዎችን፣ የዋናውን መስመር ደህንነት የሚደግፉ የሐዲድና የጣቢያዎች ዕቃዎችን ያካትታል።