በትግራይ ክልል የሚገኘውን የቀድሞ ታጣቂዎች ተሀድሶና መልሶ ማቋቋም ስልጠና ማዕከል 5 ሺህ 500 የቀድሞ ታጣቂዎች የተሀድሶ ስልጠና እየወሰዱ መሆኑ ተገልጿል።
በክልሉ ቀደም ሲል የተሀድሶና መልሶ ማቋቋም ስልጠና ሲሰጥበት የቆየው የመቀሌ ማዕከል የቀድሞ ታጣቂዎችን ተቀብሎ እያስተናገደ እንደሚገኝ የተገለጸ ሲሆን ዲፕሎማቶችና የዓለም አቀፍ ተቋማት ተወካዮች ማዕከሉን ምልከታ ማድረጋቸው ተገልጿል።
የተባበሩት መንግሥታት ተወካዮችና በኢትዮጵያ የተለያዩ ሀገራት አምባሳደሮች በትግራይ ክልል የሚገኘውን የቀድሞ ታጣቂዎች ተሀድሶና መልሶ ማቋቋም ስልጠና ማዕከል የጎበኙ ሲሆን በአሁኑ ወቅት 5 ሺህ 500 የቀድሞ ታጣቂዎች በማዕከላቱ የተሀድሶ ስልጠና እየወሰዱ ይገኛሉ ተብሏል።
በጉብኝቱ የብሔራዊ ተሀድሶ ኮሚሽን ኮሚሽነር ተመስገን ጥላሁንን ጨምሮ የኮሚሽኑ አመራሮች ተገኝተዋል።