EthiopiaNews

የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ ግዴታቸውን ያልተወጡ የደረጃ ሀ ግብር ከፋዮች እስከ ህዳር 2 ቀን 2019 ዓ.ም ድረስ የሂሳብ መዝገባቸውን በኦንላይን እንዲያቀርቡ በድጋሚ አሳሰበ።

ቢሮው ይሄን ያለው ግዴታቸውን ያልተወጡ ግብር ከፋዮችን በተመለከተ ባወጣው መግለጫ ነው።

ቢሮው እስከ ህዳር 2 ቀን 2019 ዓ.ም ድረስ የሚቀርቡ የሂሳብ መዝገቦችም በሕጉ መሠረት ቅጣት ተጥሎባቸው እንደሚስተናገዱም ገልጿል።

ቢሮው ከህዳር 3 ቀን ጀምሮ ግን የሂሳብ መዝገብ እንደማይቀበል አስታውቋል።

ከህዳር 3 ቀን 2019 ዓ.ም ጀምሮ ሂሳብ መዝገባቸውን ባላቀረቡ ግብር ከፋዮች ላይ ቢሮው ባለው መረጃ መሠረት ውሳኔ በማውጣት ዓመታዊ ግብሩን ከነቅጣቱ የሚያስከፍል መሆኑን ገልጿል።

በኦንላይን ግብራቸውን አሳውቀው ክፍያ ያልፈፀሙ ግብር ከፋዮችም በነዚህ ሁለት ቀናት ውስጥ ግብራቸውን እንዲከፍሉ ቢሮው አሳስቧል።