EthiopiaNews

በኢትዮጵያ የአውሮፓ ህብረት አምባሳደር ሶፊ ፍሮም ኤሜስቤርገር ህብረቱ በፈረንጆቹ 2025 አመት ከኢትዮጵያ 1 ነጥብ 3 ቢሊየን ዩሮ ምርት ማስገባቱን ተናገሩ።

ኢትዮጵያ ወደ ውጭ ሃገራት ከምትልከው 22 በመቶ ምርት ወደ አውሮፓ ህብረት ሀገራት የሚገባ መሆኑን የጠቀሱት አምባሳደሯ ኢትዮጵያ ወደ ህብረቱ ከተላከቻቸው ምርቶች 371 ሚሊየን ዩሮ ገቢ ማግኘቷንም ካፒታል ጋዜጣ ላይ ባሳተሙት ጽሁፍ አስፍረዋል፡፡

ያለ ታሪፍ ወደ አውሮፓ ህብረት ምርቶችን እንዲያስገቡ ከተፈቀደላቸው 33 የአፍሪካ ሃገራት መካከል አንዷ ኢትዮጵያ መሆኗን የገለጹት አምባሳደሯ የአፍሪካ ሃገራት በፈረንጆቹ 2025 አመት 182 ቢሊየን ዩሮ ምርት ወደ አውሮፓ መላካቸውን አክለው ገልፀዋል።