በአሜሪካ የኢትዮጵያ ኤምባሲ የኢትዮጵያን ቡና የሚያስተዋውቅ (ቴስት ኦፍ ኢትዮፕያን ኮፊ ) የተባለ ፌስቲቫል ዋሽንግተን ዲሲ በሚገኘው የኤምባሲው ቅጥረ ግቢ መካሄዱን አስታወቀ።
ኤምባሲው ይሄን ያለው ባወጣው መግለጫ ነው።
ፌስቲቫሉ የኢትዮጵያን ምርት እና አገልግሎት ለአሜሪካዊያን ዜጎች እና የቢዝነስ ማህበረሰብ የማስተዋወቅ እና የገበያ ትስስር ለመፍጠር ያለመ መሆኑን ነው ኤምባሲው ያስታወቀው።
ከኢትዮ-አሜሪካ ንግድ ምክር ቤት፣ ትዉልደ ኢትዮጵያዉያን፣ አሜሪካውያን ዜጎች፣ ከኢትዮጵያ ዳያስፖራ የንግዱ ማህበረሰብ አባላት፣ የሚዲያ ባለሙያዎች እና የማህበራዊ ሚዲያ አንቂዎችን ጨምሮ ከ300 በላይ እንግዶች በፌስቲቫሉ ተሳትፈዋል።በአሜሪካ የኢትዮጵያ ኤምባሲ የኢትዮጵያን ቡና የሚያስተዋውቅ (ቴስት ኦፍ ኢትዮፕያን ኮፊ ) የተባለ ፌስቲቫል ዋሽንግተን ዲሲ በሚገኘው የኤምባሲው ቅጥረ ግቢ መካሄዱን አስታወቀ።
ኤምባሲው ይሄን ያለው ባወጣው መግለጫ ነው።
ፌስቲቫሉ የኢትዮጵያን ምርት እና አገልግሎት ለአሜሪካዊያን ዜጎች እና የቢዝነስ ማህበረሰብ የማስተዋወቅ እና የገበያ ትስስር ለመፍጠር ያለመ መሆኑን ነው ኤምባሲው ያስታወቀው።
ከኢትዮ-አሜሪካ ንግድ ምክር ቤት፣ ትዉልደ ኢትዮጵያዉያን፣ አሜሪካውያን ዜጎች፣ ከኢትዮጵያ ዳያስፖራ የንግዱ ማህበረሰብ አባላት፣ የሚዲያ ባለሙያዎች እና የማህበራዊ ሚዲያ አንቂዎችን ጨምሮ ከ300 በላይ እንግዶች በፌስቲቫሉ ተሳትፈዋል።
በአሜሪካ የኢትዮጵያ ልዩ መልእክተኛና ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ብናልፍ አንዱአለም ቡና ለኢትዮጵያዊያን የእለት-ተዕለት ኑሮ አንስቶ በማህበራዊ ግንኙነት ያለውን ጥብቅ ቁርኝት በመግለጽ የኢትዮጵያ ቡና ለሃገራዊ ኢኮኖሚ ያለዉን ፋይዳ እና ከሌሎች ሀገራት ቡና ጋር ሲነፃፀር ያሉትን ልዩ የጣዕምና የጥራት ተምሳሌትነት ለታዳሚዎች ገለጸዋል።
በተጨማሪም ትዉልደ ኢትዮጵያዊያን በሚኖሩበት አካባቢ ባላቸዉ የንግድ እንቅስቃሴ የኢትዮጵያን ባህል፣ ምርት እና አገልግሎት ለሌሎች ሃገራት በማስተዋወቅ ሁሉም ለሀገሩ አምባሳደር መሆኑን የሚያሳይ እንደሆነ በመግለፅ በቀጣይም የትውልድ ሀገራቸውን ምርትና አገልግሎቶች ለአሜሪካውያን በስፋት በማስተዋውቅ ሀገራዊ ሃላፊነታቸዉን እንዲወጡ ጥሪ አቅርበዋል።