EthiopiaNews

የከተማ አስተዳደሩ ገቢዎች ቢሮ ከህዳር 15 ቀን 2019 ዓ.ም በኋላ በኦንላይን የሚላኩ የደረጃ ሀ ግብር ከፋዮች የሂሳብ መዝገቦችን እንደማይቀበል አስታወቀ።

ቢሮው ይሄን ያለው ባወጣው መግለጫ ነው።

ቢሮው የደረጃ ሀ ግብር ከፋዮች በኦንላይን የሂሳብ መዝገቦቻቸውን የሚያሳውቁበት የመጨረሻ ቀን ትናንት ህዳር 15 ቀን 2019 ዓ.ም መጠናቀቁን ገልጿል።

በመሆኑም ከህዳር 15 ቀን 2019 ዓ.ም በኋላ በኦንላይን የሚላኩ የሂሳብ መዝገቦችን ቢሮው እንደማይቀበል በመግለፅ ዓመታዊ ግብሩን ባለው መረጃ በማስላት በተጨማሪም ሂሳብ መዝገብ ባለማቅረብ ምክንያት በታክስ አስተዳደር አዋጁ 983/2008 አንቀፅ 102 እና 110 እንዲሁም በተሻሻለው የታክስ አስተዳደር አዋጅ 1434/2018 መሰረት የተጣሉ ቅጣቶች በመጨመር ጭምር ግብሩን የሚያስከፍል መሆኑን አስታውቋል።

ቢሮው በርካታ ግብር ከፋዮችም የሂሳብ መዝገባቸውን በኦንላይን በመላክ ዓመታዊ ግብራቸውን ያሳወቁ መሆኑን አስታውሷል።