የአፈ-ጉባዔዎች የምክክር መድረክ በላሊበላ ይካሄዳል
ፌዴራል እና የክልል አፈ-ጉባዔዎች የምክክር መድረክ ከነገ ጀምሮ በላሊበላ ከተማ ይካሄዳል፡፡
የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ-ጉባዔ ታገሠ ጫፎ እና ምክትል አፈ-ጉባዔ ሽታዬ ምናለ ላሊበላ ገብተዋል።
የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ-ጉባዔ አደም ፋራህ እና ምክትል አፈ-ጉባዔ ዕፀገነት መንግስቱ እንዲሁም የክልል አፈ-ጉባዔዎች ላሊበላ ከተማ ሲደርሱ አቀባበል ተደረጎላቸው፡፡
የላሊበላ ከተማ ከንቲባ አቶ ይልማ መርቅ ለአፈ- ጉባዔዎቹ ልኡካን አቀባበል አድርገውላቸዋል።
አፈ-ጉባዔዎቹ ከአቀባበል ሥነ-ሥርዓቱ በኋላ ከሌሎች የመንግስት የሥራ ኃላፊዎች ጋር በመሆን የላሊበላ ውቅር አብያተ-ክርስቲያናትን ጎብኝተዋል፡፡
በዚሁ በላሊበላ ከተማ የፌዴራል እና የክልል አፈ-ጉባዔዎች የምክክር መድረክ ከነገ ጀምሮ እንደሚካሄድ ከህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።